CLOSED
ዋን ኤከር ፈንድ በአማራ ክልል የእርሻ ግብአቶችን ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ለማከራየት ለሚፈልጉ አቅራቢዎች የወጣውን ጨረታ እንዲጫረቱ ይጋብዛል
OA
One Acre Fund
Government Organization
Location
Amhara
Category
IT & Software
Reference Number
CHR-008773
Tender Type
Open
Description
የትንስፖርት አገልግሎት ለማግኘት የወጣ ጨረታ ዋን ኤከር ፈንድ በአማራ ክልል የእርሻ ግብአቶችን ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ተሽከርካሪዎችን ለማከራየት ለሚፈልጉ አቅራቢዎች የወጣውን ጨረታ እንዲጫረቱ ይጋብዛል። እንደ የእርሻ መሳሪያ እና ዘር ያሉ ግዙፍ መጠን ያላቸውን ግብአቶች ወደ ወረዳ ማዕከል ከተሞች ለማጓጓዝ ስለምንፈልግ የተለያየ መጠን ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ማቅረብ የሚችል አቅራቢ ነጋዴ እንፈልጋለን። ሁሉም ነጋዴዎች ለሁሉም ተሽከርካሪዎች የንግድ ስራ ፈቃድ፣ ሊብሬ፣ የመንጃ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት እና የታደሰ ቦሎ ሊኖራቸው ይገባል። ነጋዴዎች ገንዘብ የሚከፈላቸው በባንክ በኩል ይሆናል። በባንክ ሒሳቡ ላይ ያለው ስም የንግድ ስራ ፈቃድ ከተሰጠው ስም ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት። (ይህ ካልሆነ ነጋዴው የውክልና ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።) ነጋዴው መጫረት የሚፈልገው ከ200,000 ብር በላይ በሚጠይቅ ጉዞ ላይ ከሆነ (የረጅም ርቀት ከባድ መኪና ከሆነ) የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው። በምትጫረቱበት ጊዜ ለምታጫርቱት ተሽከርካሪ ቀጥተኛ ሃላፊነት ሊኖራችሁ ይገባል። የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ለማግኘት ወደ ተለያየ መስመር የሚደውል ሶስተኛ ወገን እንዲኖር አንፈልግም። በመሆኑም ወደ ብዙ የጉዞ መስመሮች የሚጫረት ተጫራች የማሸነፍ እድሉ ዝቅተኛ ነው። ይህ ለተሽከርካሪው ቀጥተኛ ሃላፊነት አለመኖሩን ያሳያል። እባክዎ የሚላክለዎትን የጨረታ ሰነድ በመሙላት ማህተም እና ፊርማ በማስቀመጥ ከሚከተሉት ውስጥ በአንዱ አማራጭ ይላኩ። ኢሜይል፦ ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org የቲሌግራም አካውንት፦ @oafbidsubmissions የጨረታው የመጨረሻ ቀን:- ነሃሴ 26 2018 ለተጨማሪ መረጃ እና የጉዞ መስመሮች ዝርዝር ለማግኘት በዚህ ስልክ ይደውሉ፡ 0985654565 0984784748 የምናጓጉዝባቸው የጉዞ መስመሮች ዝርዝር ከላይ በተቀመጠው ስልክ በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡ አንዳንድ መስመሮች ተሽከርካሪው የሚቆምባቸውን እና የሚያራግፍባቸውን ቦታዎች ያካትታሉ። መጫረት ለምትፈልጉት ለእያንዳንዱ የጉዞ መስመር በምታቀርቡት ተሽከርካሪ የጭነት መጠን ትይዩ ላይ መጫረት የምትፈልጉትን ዋጋ ጻፉ። ጨረታውን በቀጥታ ማቅረብ በምትችሉት ተሽከርካሪ መስመር ብቻ ጻፉ። ማስታወሻ፦ ብዙ አርሶ አደሮች ግብአቶች ከዋን ኤከር ፈንድ በወቅቱ እንዲደርሳቸው ይጠባበቃሉ። በመሆኑም እንዳንዘገይባቸው የሎጂስቲክስ ስራችንን በጥንቃቄ እናቅዳለን። በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት የሚያከናውኑንልንን አጋሮች እንፈልጋለን። ዋን ኤከር ፈንድ ከእያንዳንዱ ማጓጓዝ 2 ሳምንታት ቀደም ብሎ ለሁሉም አቅራቢ ነጋዴዎች የማጓጓዝ እቅድ ይልካል። በኢዝያን ጊዜ ነገዴዎቹ ስለጉዞ አስተያየት መስጠት ወይም ጥያቄ መጠየቅ ይችላሉ። ዋን ኤከር ፈንድ ከማጓጓዝ 2 ቀን ቀደም ብሎ ነጋዴዎቹ በተስማሙት መሰረት ተሽከርካሪዎችን በተሰጣቸው የጉዞ መስመር ላይ ለማቅረብ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ነጋዴው ስለጉዞ ካረጋገጠ በኋላ ተሽከርካሪውን ማቅረብ ካልቻለ ዋን ኤከር ፈንድ ውሉን ሙሉ በሙሉ ሊያቋርጥ ይችላል። ዋን ኤከር ፈንድ ጥብቅ የሆነ የጸጥታ ፖሊሲ አለው። በመሆኑም ግጭት ባለባቸው መንገዶች ጉዞ እንዲያደርጉ ነጋዴዎችን አይጠይቅም። ነጋዴው መንገዱ የጸጥታ ችግር እንዳለበት ካመነ ከዋን ኤከር ፈንድ ጋር በመነጋገር ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ስምምነት ላይ መድረስ አለበት።
Source
Source Link Available for Members
Sign up free to access the original tender posting and full details
Important Dates
Published
August 28, 2026
Closing Date
September 1, 2026
Closed 10 days ago
Contact Information
Organization
████████████████
Phone
+251 ██ ███ ████
████@████.gov.et
Login to view
Similar Tenders
Ethio telecom invites eligible bidders for the procurement of rental vehicles for the Central North Region (Debre Berhan) and its working boundaries under RFQ No. 4287190.
Ethio Telecom
Closes in 16 days
View Details
Plan International Ethiopia, Amhara PA is seeking competent and reliable suppliers for a Long Term Agreement to provide two buses (44 seats and above) including fuel costs.
Plan International Ethiopia, Amhara Program Area
Closes in 5 days
View Details
MOENCO is inviting sealed bids for the supply and delivery of IT equipment.
MOENCO
Closes in 9 days
View Details